መዝሙረ ዳዊት 128:1-6 AMH1962 - Bible AI

1የመዓርግ መዝሙር።
እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።

2የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይሆንልሃል።

3ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።

4እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።

5እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ።

6የልጆችህንም ልጆች ታያለህ። በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን።