መዝሙረ ዳዊት 131:1-3 AMH1962 - Bible AI

1የዳዊት መዓርግ መዝሙር።
አቤቱ፥ ልቤ አይታበይብኝ፥ ዓይኖቼም ከፍ ከፍ አይበሉብኝ፤ ከትልልቆች ጋር፥ ከእኔም ይበልጥ ከሚከበሩ ጋር አልሄድሁም።

2ነፍሴን አሳረፍኋት፥ የእናቱንም ጡት እንዳስተውት ዝም አሰኘኋት፤ ነፍሴ የእናቱን ጡት እንዳስተውት በእኔ ውስጥ ናት።

3ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እስራኤል በእግዚአብሔር ይታመን።